top of page

Hon. Dr. Haddis Alemayehu's Short Biography

የክቡር ዶ/ር ሀዲስ ዓለማየሁ  አጭር የህይወት ታሪክ

HA Photo 2.jpg

ደራሲ ዶ/ር ሀዲስ ዓለማየሁ (ሃዲስ ኣለማየሁ) ከአባታቸው ከቄስ ዓለማየሁ ሰለሞን እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ደስታ ዓለሙ በደብረ ማርቆስ አውራጃ በጎዛመን ወረዳ በእንጾር ኪዳነ ምኅረት ቀበሌ በጥቅምት ፯ ቀን ፲፱፻፪ ዓ.ም ተወለዱ። 

ገና በጨቅላ እድሜያቸው በቤተ ክርስቲያን የሚሰጠውን ትምህርት በቤተሰባቸው አጠገብና ባባታቸው አገር ደብረኤልያስ ሄደው የግእዝ ትምሕርት ቤት ቅኔ ተቀኝተዋል። የቤተክርስቲያን ስርዐታትንና መንፈሳዊ ትምህርትን በጎጃም ገዳማት በደብረ ኤልያስ፣በደብረ ወርቅና በዲማ ከቀሰሙ በኋላ ወደ በ፲፱፻፲፰ ዓ.ም. አዲስ አበባ በመሄድ በስዊድን ሚሽነሪ ትምህርት ቤት በኋላም በራስ ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን ተከታተሉ። 

 

ለትንሽ ጊዜ በአስተማሪነት ሥራ ተሰማርተው እንዳገለገሉ የፋሽስት ጣሊያን ወረራ ተከሰተ።

 

የኢጣልያ ወረራ ሲከሰት ከልዑል ራስ ዕምሩ ኃይለ ሥላሴ ጦር ጋር በምዕራብ ኢትዮጵያ በአርበኝነት ሲዋጉ ቆይተው በመያዛቸው ጣሊያን ከልዑል ራስ ዕምሩ ጋር በግዞት ለሰባት ዓመታት በፖንዞ ደሴትና በሊፓሪ ደሴት ታስረው ቆይተዋል።

ከዚያም የተባባሪ ኃያላት ወታደሮች በ1935 ዓ.ም. ሲያስመልጧቸው በተመለሱበት ጊዜ በትምህርታቸው እንደገና #በኦክስፎርድ ከገፉ በኋላ በተለያዩ የመንግስት ተቋማት በተለይም በትምህርት ሚኒስቴር ለረጅም ጊዜ አገልግለዋል።

ደራሲ ዶ/ር ሀዲስ ዓለማየሁ በርካታ የስነጽሑፍ ሥራዋችን አበርክተዋል። ከነዚህም ውስጥ ታላቅ አድናቆትንና እውቅናን ያተረፈው ሥራቸው #ፍቅር_እስከ_መቃብር (1958) በሁለት የተለያዩ መደቦች ውስጥ የሚገኙ የሁለት ሰዎች የፍቅር ታሪክ ላይ ሲያተኩር፤ በጊዜው የነበረውን ወግና ልማድ ይገልጻል። 

 

እንዲሁም በ1970 ወንጀለኛው #ዳኛ በ 1980 ደግሞ ስለ ማህበራዊ ጉዳዮችና ስለ ጣሊያን ውርስ የሚዳስሰውን #የልም_እዣት የተሰኙትን ልብ ወለድ ታሪኮች ለንባብ አቅርባዋል።

ዚህ ባሻገር:

 

  • የአበሻና የወደኋላ ጋብቻ - ተውኔት

  • ተረት ተረት የመሰረት

  • ትዝታ

  • የተሰኙት ጽሁፎችና የሌሎች በርካታ ሥራዎች ባለቤት ናቸው።

 

በ 1974 አርቲስት ወጋየሁ ንጋቱ ፍቅር እስከ መቃብርን በኢትዮጵያ ራድዮ ግሩም አርጎ ከተረከዉ ወዲህ መጽሐፉ በኢትዮጵያዉያን ልብ ዉስጥ ተቀመጠ ወጋየሁንም ከጫፍ እስቀጫፍ አስተዋወቀ ለዚህ ብዕረኛዉ ሀዲስ አለማየሁ መጽሐፉን እኔ ጻፍኩት እንጂ መጽሐፉ ያንተ ነዉ ብለዉ መጽሐፋቸዉ ላይ ጽፈዉና ፈርመዉ እንደሰጡት ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ ተናግሮአል።

 

ዘመን የማይሽረዉ ብዕረኛ በኢትዮጵያ የሥነ-ጽሑፍ ታሪክ ወደር የማይገኝለት የልቦለድ መጽሐፍ «ፍቅር እስከ መቃብር»  ሁላችሁም እንደምታስታውሱት ሙዚቀኛ #ቴዲ_አፍሮም በዚህ ልብ ወለድ በፍቅር ወድቆ በዜማ ደራሲዉን #ማር_እስከ_ጧፍ በሚለዉ ዜማዉ ሕያዉ ማድረጉ ይታወሳል።

HA-Photo 1.jpg

ለክብር ዶ/ር ሀዲስ ዓለማየሁ (1902 ዓ.ም. -1996 ዓ.ም.) መታሰቢያ የቆመ ከነኀስ የተሠራ ኃውልት፤ ቅዳምን ገበያ - ደብረ ማርቆስ፤ ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 28/2009 ዓ.ም.ነው። 

ደራሲ፣ ዲፕሎማት፣ አርበኛ፣ መምህር የክብር ዶክተር ሀዲስ ዓለማየሁ ከነኀስ የተሠራ ኃውልት የቆመላቸው — ጥቅምት 5/1902 ዓ.ም. ተወልደው ኅዳር 26/1996 ዓ.ም. ላረፉት ለሀዲስ ዓለማየሁ ደብረ ማርቆስ ከተማ ላይ ነው::

ለክብር ዶክተር ሀዲስ ዓለማየሁ የኢትዮጵያ ደራሲያን ማኅበር ያዘጋጀው የፖስታ ቴምብር በኢትዮጵያ የፖስታ ድርጅት በ2002 ዓ.ም. ታትሞ ተሠራጭቷል፡፡

«የአበሻና የወደኋላ ጋብቻ፣ ተረት ተረት የመሠረት፣ ፍቅር እስከ መቃብር፣ ወንጀለኛ ዳኛ፣ የልም ዣት፣ ትዝታ» የሀዲስ ዓለማየሁ አዕምሮ ውልዶች ናቸው፡፡

የክብር ዶክተር ሀዲስ ዓለማየሁ በሕይወት ሳሉ ያላሣተሟቸው ግጥሞቻቸውን የያዘ በዶ/ር ታየ አሰፋ የተዘጋጀና በደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የሀዲስ ዓለማየሁ ጥናት ተቋም ዓመታዊ ጉባዔ ታትሞ እንዲወጣ ሲሆን ደራሲው ትምህርትና ተማሪዎች የሚል መፅሃፍም አላቸው :: 

ደራሲ ዶ/ር ሀዲስ ዓለማየሁ በኢትዮጵያ የስነ ጽሑፍ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽዖ በማበርከታቸው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ #የዶክቶርነት ማዕረግ ተሰጥቷቸዋል። ደራሲው በኅዳር 26 ቀን 1996 ዓ.ም. በ94 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

bottom of page